ኮሌጁ ዋና ቁልፍ ተግባሩንና ሁለቱን አብይ የትኩረት መስኮች በማሳካት ሂደት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓቱ የሚመራበት መርሆዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡-
ተቋማት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላት እንዲሆኑ ማድረግ፣
በገበያ ፍላጎት የሚመራ ስልጠና እንዲኖር ማድረግ፣
ተቋማት ብቁ የሰው ኃይል መፍሪያና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መፈልፈያ እንዲሆኑ ማድረግ፣
ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ራሱን የሚያስተካክል የሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት፣
ተለማጭ የሆነ የትምህርትና ሥልጠና አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት፣
ያልተማከለ ሥርዓት መዘርጋት፣የተቀናጀና የተዋሃደ ሥርዓት መዘርጋት፣
የትብብር ሥልጠናን ማስፋፋት፣
የባለድርሻዎችን የቴክኖሎጂ ሠራዊት ክንፎች ተሳትፎ ማሳደግ፣