የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሌጅ ከኮሌጁ አካዳሚ ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ ።

(መሰከረም 09/2018ዓ.ም )የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ከኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ጋር መወያየቱን ተገለፀ ።
በውይይቱም የ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካለንደር ማፅደቅ ፣የትምህርት ምዝገባ ቀን መወሰን ፣የኦን ላይን ምዝገባ የሚሉ አጀንዳዎች ቀረበው ተወያይቶበታል ።
በውይይቱም የ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካለንደር መሠረት ፣የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ወሰነ ትምሀርት መቼ እንደሚጀመር እና እንደሚያበቃ ኮሚሽኑ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ።
የ1ኛ ወሰነ ትምህርት ምዝገባ
• ከመስከረም 19__23/01/2018ዓ.ም የምዝገባ ቀን ስሆን (መደበኛ ምዝገባ ክፍያ 500ብር)
• ከመስከረም 26__28/01/2018ዓ.ም የቅጣት ጊዜ ይሆናል (1, ቀን 100ብር 2,ቀን 200ብር 3,ቀን 300ብር )ይቀጣል ።
• ከመስከረም 26/01/2018ዓ.ም እሰከ ጥር 29/05/2018ዓ.ም መደበኛ የትምህርት ጊዜ ይሆናል
• የሠልጣኞች እረፍት ጊዜ ከየካቲት 02__06/06/2018ዓ.ም ይሆናል
የ2ኛ ወሰነ ትምህርት ምዝገባ
• ከየካቲት 09__11/06/2018ዓ.ም ይሆናል ፣
• ከየካቲት 12__14/6/2018ዓ.ም የቅጣት ጊዜ ይሆናል ፣
• ከየካቲት 09/06/2018ዓ.ም እሰከ ስኔ 30/10/2018ዓ.ም መደበኛ ትምህርት የሚጠናቀቅበት ጊዜ መሆኑን በካለንደሩ መሠረት የኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን አፅድቋል ፣
በዚሁ መሠረት ሠልጣኞች የመመዝገቢያ ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኮሌጁ የውስጥ ገቢ አካውንት በመከፈል ስሊፕ/ደረሰኝ /ብቻ ይዘው እንዲመዘገቡ ጭምር ወሰኗል።
በሌላ በኩል ኮሌጁ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለመሄድ በቅርብ ጊዜ የኦን ላይን ምዝገባ ለማስጀመር ኮሌጁ እየሰራ እንደሚገኝ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ ያስታውቃሉ ።
ማሳሰቢያ
የኮሌጁ የዉስጥ ገቢ አካውንት ቁጥር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000148256016 መሆኑን እናሳውቃለን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *