(ግንቦት 20/9/2017ዓ.ም ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ክቡር አቶ ሀብታሙ አለነ የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የተቋሙ ሁኔታ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ።
በጉብኝቱም ከዚህ በፊት በተከሰተው የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የወደሙ ንብረቶች ፣ተቋሙ ያጋጠመው ችግሮች ለችግሮቹም መፍተሔ ለመሰጠት ያመች ዘንድ ከቢሮው ባለሙያዎች ጋር በመሆን ተቋሙን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ።
በሌላ በኩልም በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ቢሆንም ፣ በተቋሙ በኩል መፍታት ያለበት ችግሮች ተቋሙ መፍታት እንደለበት ጠቅሶ፣ ከክልል ጋር በመሆን መፍታት ያለበት ችግሮች በጋራ በመሆን መፍትሔ መሰጠት እንዳለብን ክቡር አቶ ሀብታሙ ገልጿል ።
