HOME

 

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ

የካማሺ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን

እንኳን ደህና መጣቸሁ

የአሁኑ የካማሺ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በህዳር ወር 25/1996 ዓ/ም ተገንብቶ በቀድሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፓብልክ ፕረዝዴንት በአቶ ግርማ ወ/ጊዮርግስ አነስተኛ የዕደ-ጥበባት ሙያን ለማስፋፋት የተገነባ ማዕከል በማለት ተመርቆ በርከታ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ካደገበት እስከ 28/03/2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በ10 የተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ከደረጃ 2 እሰከ ደረጃ 4 ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በዞኑ ማህበብረሰብ ፍላጎት የተነሳ ኮሌጁ ጥናት በማካሄድ ተጨማሪ 3 ዲፓርትሜንቶች እንድከፈቱ ተደርጎ እንዲሁም በዳረጃ 5ትም በኮሌጁ ስልጠና እንድሰጥ ተፈቅዶልን ከቀን 29/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ ኮሌጁ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ማደጉ የተሰማኝ ደስታ እየገለጽኩ ኮሌጁ ከዚህ በኃላ ለዞኑ ማህብረሰብና ለአጎረባች አካባቢዎች በርታ ችግር ፈቺ ሥራዎች እንደሚሰራም ጭምር አደራ አለበት፡፡
በዚህ አገጣሚ ለኮሌጁ ማህብረሰብ በሙሉ በርትቶ የመስራት መልዕክት አስተላልፋለሁ፡፡
ኮሌጁ በካማሺ ዞን፣ በካማሺ ከተማ አስተዳደር ግዛት ዉስጥ የሚትገኝ ሲትሆን በዞኑ ላሉት 5ቱ ወረዳች እና ለካማሺ ከተማ አስተዳደር ማህብረሰብ እንዲሁም ለአጎራባች አካባቢ ማህብረሰብም ጭምር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡