የካማሺ ቴክኒክና ሙያትምህርት ስልጠና ኮሌጅ 5ባለ 2 ተገጣጣሚ የብረታ አልጋና ፍራሽ ገዝቶ ለ10 ታራሚ ሴቶች በስጦታ መልክ መብረከቱን ተገለፀ ።

(ነሐሴ 27/2017ዓ.ም )የካማሺ ቴክኒክና ሙያትምህርት ስልጠና ኮሌጅ 5ባለ 2 ተገጣጣሚ የብረታ አልጋና ፍራሽ ገዝቶ ለ10 ታራሚ ሴቶች በስጦታ መልክ መብረከቱን ተገለፀ ።
በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን ኮሌጇ ከመደበኛ ስራ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ስራዎችም ጭምር እየሰራ መሆኑን የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ አስታወቁ ።
በፕሮግራሙ ላይ የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፣የከማሺ ዞን ም/አስተዳዳሪ ፣የካማሺ ዞን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ፣የካማሺ ዞን ገ/ ኢ/ል/መምሪያ ሃላፊ ፣የዞኑ ንግድ መምሪያ ሃላፊ ፣የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝቶበታል ።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ብጅጋ እንደገለፁት የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በማዘጋጀት ለካማሺ ማረሚያ ቤት ለ10 ታራሚ ሴቶች 10 አልጋና 10 ፍራሽ በስጦታ መልክ መሰጠቱን እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሶ ፣በአሁኑ ጊዜ እንደመንግስትም ሆነ እንደ ፓርቲ በሀገሪቱ ደረጃ በክልልም አልፎ እሰከ ወረዳ ድረስ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየተሰራ መሆኑን ይገልፃሉ ።
በዚሁ መሠረት የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ለዞኑ ማረሚያ ቤት ያበረከተው አስተዋጽኦ ከመቶ ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መሆኑን ጠቅሶ ፣እንደዚህ አይነት መልካም ስራዎች መስራት እጅግ የሚበረታታ መሆኑን ክቡር አቶ ብጅጋ ይገልፃሉ ።
በዚህም አጋጣሚ ሌሎች ተቋማት ከኮሌጁ ልምድ ወሰደው ለአቅመ ደካሞች በጎ ተግባር ማድረግ እንዳለባቸው ክቡር አቶ ብጅጋ አሳስቧል ።
የከማሺ ማረሚያ ቤት መምሪያ ሃላፊ ኮ/ር ማሞ አዳልም ለታራሚ ሴቶች በኮሌጁ የተደረገው ድጋፍ በራሱ በዞኑ ማረሚያቤት ስም እጅግ አመሰግኗል ።
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ በንግግራቸው እንደ ገለፁት ለሰው መልካም ማደረግ ከፈጣሪ ዘንድም ተቀባይነት ያለው ነገር ነዉ ።በአጋጣሚ ስህተት ሰርተዉ በህግ ጥላ ስር ቢጠለሉም እንኳ ሰው መሆናቸው ማሰብ ተገቢ ነዉ ።ስለዚህ ለእነዚህ 10 ታራሚ ሴቶች 10 አልጋ እና 10 ፍራሽ በቂ ባይሆንም አቅማችን የቻለው ያህል ድጋፍ ማድረጋችን ተገቢ መሆኑን የካማሺ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ ይገልፃሉ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *