(ነሐሴ 29/2017ዓ.ም )የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የቀረበው የጥናትና ምርምር ፀሑፍ በኮሌጁ ቦርድ አባላት መፅደቁን ተገለፀ ።
የካማሺ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ በ2017ዓ.ም የተጠና የድህረ ምረቃ ጠቋሚ ጥናት ሰነድ ለኮሌጁ ቦርድ አባላት ማቅረቡን የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ምህረት አድማሱ አስታወቁ ።
አቶ ምህረት በንግግራቸው እንደገለፁት ጥናቱ አለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረውና የሀገሪቱንና የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሰራርን ተከትሎ እንዲጠና የበኩላችንን ድርሻ በማወጣት የሰከነና የጠራ ግንዛቤ በመያዝ የጥናቱን አርስት በመምረጥ የጥናቱን ዳራ ጠንቅቆ በማወቅ ለጥናቱንም መነሻ የሆኑትን ችግሮች ተንትኖ በማስቀመጥ ፣የጥናቱን ዓላማ ጠንቅቆ በመገንዘብ ፣የጥናቱን አላማና አስፈላጊነት በማስቀመጥ ፣ ተዓማኒነት እንዲኖረው ተደረጎ የተጠና ስሆን ፣ለተለዩ ችግሮች የመፍተሔ ሀሳብ እንዲያገኝ ፣ጥናቱ እንዲፀድቅ ለቦርድ አባለት አቅርቧል ።
የቦርድ አባላትም በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ትክክለኛና አሳማኝ ጥናት መሆኑን እንዲፀድቅ ሀሳብ አስተያየታቸውን አንስቷል ።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ብጅጋ ፃፊዮ በባኩላቸው ፣ኮሌጁ ያቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ የዞኑን ተጭባጭ ሁኔታ የሚገልጽ ከመሆኑም ባሸገር ፣ኮሌጁ በጥናቱ ያካተተው የጥናት አርስቶች ኮሌጁ እንዲሰፋፋና ከነበረበት ደረጃ ከፍ እንዲል በጥናቱ የተካተተው ስሆን፣የዚህ ዞን ቀጣይ ዘመንና የመጪው ትውልድ የሰነቀ ከመሆኑም አልፎ ፣ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አቶ ብጅጋ ይገልፃሉ ።በዚሁ መሠረት ሰነዱን ለቦርዱ አባላት በማቅረብ ያለምንም ተቃውሞ እና ታቅቦ ልዩነት በለሌዉ ድምፅ ጥናቱን አፅድቋል ።
